+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሆላንድ ኤምባሲ – ኮካ – አማኑኤል የመንገድ ጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

ግንቦት 8 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከሆላንድ ኤምባሲ ወደ ኮካ – አማኑኤል የሚወስደው አቋራጭ መንገድ የጥገና ስራ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል።

ይህ መንገድ ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚያስተናግድ እና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጠ በመሆኑ የኮብል ንጣፉ የተቦረቦረ እና ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

በአካባቢው የነበረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ችግር ለመፍታት፤ ቀደም ሲል የነበረውን የኮብል ንጣፍ ሙሉ በሙሉ በማንሳት፣ በመልሶ ግንባታ ደረጃ 473 ሜትር ርዝመት እና 15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን አስፋልት በማልበስ መንገዱን ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል፡፡

Comments are closed.