+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡና የሚያዘምኑ ሁለት ስምምነቶችን በዛሬው እለት ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአለም ባንክ በተገኘ የ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ በዛሬው እለት የተፈረመው ውል ስምምነት የመጀመርያው ለከተማው የሚመጥኑ ዘመናዊና ለአገልግሎት ተስማሚ የሆኑ 110 ባሶችን ከቻይናው ዩቶንግ ባስ ካምፓኒ ጋር ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግዥ ለመፈፀም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ኩባንያው ባሶቹን በ8 ወራት ውስጥ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ሁለተኛው ስምምነት ደግሞ የአንበሳ አውቶብስን አቅም የሚያዘምነውና የሚያሳድገው በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን የታገዘው የብልህ ትራንስፖርት ስርዓት (intelligent transport system) ከቻይናው ሺንዶ ሂሰንስ ትራንስ ቴክ ኩባንያ ጋር የተፈፀመ ውል ነው፡፡ይህም ውል ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ እና በሃገር ውስጥ በተጨማሪ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግ ሲሆን አጠቃላይ ድርጅቱን አለም ከደረሰበት የትራንስፖርት መሰረተ ልማት እድገት ጋር የሚያቀራርብና ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት እንዲሁም ለደንበኞች በየተርሚናሉና የጉዞ ዲጂታል መረጃ አቀረርቦትም እንዲኖር የሚያደርግ ነው፡፡በዚህ የስምምነት ስነስርዓት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት በ2013 ዓ.ም ምርጫ ላይ ለህዝቡ ለመፍታት ቃል ከገባናቸው ጉዳዮች አንዱ የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎትን ማሻሻል ነበር ብለዋል፡፡በዚሁም መሰረት ባለፈው ሳምንት ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን መንገዶች መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግን ሲሆን ዛሬ ደግሞ የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያቀላጥፉና የሚያዘምኑ ስምምነቶችን ፈፅመናል በማለት ገልፀዋል፡፡እንደ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አገላለፅ የከተማ አስተዳደሩ ለከተማ ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ኪራይ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደጉም ገልፀው የትራንስፖርት አገልግሎትን መንግስት ብቻውን የሚፈታው አይደለም በማለት የግሉ ሴክተርን አስተዋፅኦ ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡እነዚህ ስምምነቶች የእውቀት ሽግግር እና ዘመናዊነትን አለም የደረሰበትን ቀልጣፋ የአይሲቲ አገልግሎትን ያካተተ መሰረታዊ የትራንስፖርት የለውጥ ስራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ስምምነቱን ከተማውን አስተዳደር በመወከል የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ ተፈራርመዋል፡፡

4 Responses to “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡና የሚያዘምኑ ሁለት ስምምነቶችን በዛሬው እለት ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *