+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣኑ ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ 111ኛ፣በኢትዮጵያ ለ46ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹ እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል መሪ ቃል በትላንትናው ዕለት አክብረዋል፡፡በዝግጅቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ ሴቶች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዓደባባይ ወጥተው መብቶቻቸውን ማስከበር ከጀመሩበት ቀን አንስቶ በኢኮኖሚውም ሆነ በአመራር ደረጃ ከፍተኛ የሆነ አወንታዊ ለውጦችን አስመዝግበዋል ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በሀገራችን ግማሽ ያህል የህዝብ ቁጥር የሚሸፍኑትን ሴቶችን በማብቃትና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በማሳተፍ ያላቸውን እምቅ አቅም እንዲጠቀሙ ማስቻል የሁላችንም የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሴቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወ/ት ፀደኒያ አበበ በበኩላቸው ሁላችንም የእህቶቻችን ጠባቂዎች ነን በምንልበት ወቅት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ፆታዊም ሆነ ማህበራዊ ጫና መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ‹‹መወለድ ቋንቋ ነው›› ያሉት ቡድን መሪዋ በስጋ እህቶቻችን ያልሆኑ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በጋራ ልንከላከልላቸው ይገባልም ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም በተያዘው በጀት ዓመት የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀው በጡረታ ለተገለሉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች የምስጋና እና የእውቅና መስጠት ስነስርዓትም ተከናውኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *