+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በሎት 5 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጉብኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት13 ቀን 2017፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በኦፕሬሽን ዘርፍ የሚያከናውነውን የራስ ኃይል የመንገድ ግንባታ ለማቀላጠፍ በዚህ በጀት ዓመት ሎት 5 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሚል ስያሜ አዲስ የመንግድ ግንባታ የሥራ ክፍል አቋቁሟል፡፡

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱን ምስረታ አስመልክቶ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ አቅም የሚያካሂደውን የመንገድ ግንባታ ሥራ አፈፃፀም ለማሳደግ እና የስራ ጫናን ለማቃለል ቀደም ሲል ከተደራጁት የመንገድ ግንባታ ሎቶች በተጨማሪ ሎት5 በሚል ስያሜ አዲስ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ማቋቋሙን ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም፤ ቀደም ሲል በስራ ተቋራጭ የግንባታ ሥራው ሲከናወን የቆየው የቦሌ አራብሳ 5 እና 6 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ በፍጥነት ባለመፈፀሙ፤ የሎት 5 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራውን ከተቋራጩ በመረከብ ግንባታውን በተሻለ አፈፃፀም እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ሠራተኞች እያሳዩት የሚገኘው የሥራ አፈፃፀም መልካም ጅምር መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤በቀጣይም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ ግንባታዎችን በማከናወን ለከተማዋ ነዋሪዎች የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የተጣለባቸውን ተልዕኮ በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.