ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት ውበትና አረንጓዴ ስራዎች በተመለከተ
የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ከማስፋፋት አንፃር፤ በግማሽ ዓመቱ አረንጓዴ ቦታዎችን ማልማትና መንከባከብብ በተመለከተ 163.1ሄ/ር አዳዲስ የመንገድ ፓርክ እና ቁርጥራጭ ቦታዎችን ማልማት ተችሏል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከእቅዳችን በላይ 26,720,918 ሚሊየን ችግኞችን መትከል የተቻለ ሲሆን አፈፃፀሙም ከባለፈዉ በጀት ዓመት ከተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9.2 (52.6%) ሚለየን ችግኝ እድገት አሳይቷል፡፡
በዚህም የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን በ2010 ከነበረበት 2.8% ወደ 20% እንዲደርስ ውጤታማ ስራዎች ተከናውኗል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
