+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት የቤት መሰረተ ልማትን በተመለከተ

👉ከቤቶች ልማት አንጻር በበጀት ዓመቱ የከተማዋን የቤት አቅርቦት ለማሻሻል በመንግስት አስተባባሪነት፣ በሪል ስቴት እና በግል አልሚዎች በተለያዩ መርሃ-ግብሮች 27,304 የቤቶች ተገንብተው አቅርቦት መጨመር ተችሏል፡፡

👉በልዩ ልዩ የቤት አቅርቦት አማራጮች 120,000 ( መቶ ሃያ ሺህ) ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ ከተጠናቀቁት ውስጥ በከተማችን ለሚሰሩ የህዝብ ልማት ስራዎች (ኮሪድርን ጨምሮ) ለሚነሱ የልማት ተነሺዎች እና የተለያዩ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ታሳቢ 9ሺ 20 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ተችሏል።

👉ህገ-ወጥነትን ከመከላከል አንፃር 113 የጋራ መኖሪያ ቤት፣ 71 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት፣ 172 የቀበሌ ቤት ማስለቀቅ ተችሏል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.