ከተማ አሰተዳደሩ በ6 ወራት ህዝቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ አኳያ
በበጀት አመቱ 6 ወራት ህዝብን የሰላም ባለቤት ከማድረግ አኳያ፣ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ህዝቡ በሰላም ሰራዊት ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅና ህገወጥ ድርጊቶችን የመከላከል ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ከፌዴራልና ከአጎራባች ሸገር ከተሞች ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የወንጀልና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር የወንጀል ምጣኔ ከመቀነስ አኳያ ከህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፤ከህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከኢኮኖሚ አሻጥር ከዝርፊያ ከሽብርና ደረቅ ወንጀሎች ጋር የተያያዙ ከ4687 በላይ የወንጀል ድርጊቶች ላይ የመከላከልና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ የተሰራ ሲሆን በት/ቤት ዙሪያና ከት/ት ተቋማት ውጭ የሚገኙና ለጸጥታ ስጋት በሆኑ 2919 አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ የአደባባይ ፕሮገራሞችና ኩነቶች በሰላም እንዲከበሩ ከማድረግ በተጨማሪ የከባድ ወንጀል ምጣኔ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ33 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡
የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተል፣ በመቆጣጠርና እርምጃ ከመውሰድ አንፃር 2464 ህገወጥ ግንባታዎች ላይ፣ 108 ህገ-ወጥ ንግድን፣ ህገ-ወጥ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን መቆጣጠርና ደንብ ማስከበር ተችሏል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
