+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በተመለከተ

👉የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ፦ በቂ ዝግጅት የተደረገበትና የመጀመሪያውን ኮሪደር ልማት አፈፃፀም ልምዶችንና የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮዎች ከነባራዊ ሁኔታችን ጋር በመቀመር/ በማስተሳሰር በፍጥነትና በጥራት 24/7 እየተተገበረ ይገኛል።

👉 ከልማት ተነሽዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይቶችና በመፍጠር እንዲሁም ክፍተቶችና ቅሬታዎችን ገለልተኛነት መፍትሄ የሚሰጥ አደረጃጀት በመፍጠር የተመራ ስራ ነው።

ለመኖር ምቹ ካልሆነ ጎስቋላ መኖሪያ ቤቶችና አካባቢዎች ለተነሱ ነዋሪዎች 9ሺህ የሚደርሱ የመኖሪያ ቤቶችን፣ 1,402የመስሪያ ሼዶችን፣200የንግድ ሱቆችን ፤2124የመስሪያ ቦታዎች እና ወደ 3000 የሚደርሱት ደግሞ በኢንዱስትሪ ቋሚ ስራ እድል እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም አረንጓዴና መጫዎቻ ቦታዎችን፣የጤናና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ማሟላት እንዲሁም የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን አስተላልፈናል።

👉የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባ በተሟላ የከተሜነት ፅንሰ ሃሳብና የመሰረተ ልማት ስርአት እንድትመራ የሚያደርግ ሲሆን በአጠቃላይ ስፋቱ 3515 ሄክታር የሚሸፍንና እና 136 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤በልማት ስራዎች ውስጥም የመንገድ ግንባታ፣ የአረንጓዴ ቦታዎች ግንባታ፣ የብስክሌት መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የታክሲና አውቶቢስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች፣ የህዝብ መጸዳጃ ቦታዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች፣ ደረጃውን የጠበቀ የከተማ መብራት፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማት፣ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ ስራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ አየገነባን እንገኛለን።በተያዘለት ጊዜ፣በጀት/ ወጪና ጥራት የምናጠናቅቀው ይሆናል።

👉ስራው በዋናነት በከተማው አቅም እና በጀት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ፤ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፤ የመብራት አገልግሎት እና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መሰረተ ልማታቸውን በመዘርጋትና ከተማዋን ስማርት ሲቲ በማድረግ በኩል ትልቅ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ።

👉በኮሪደር ልማት ስራችን ፦ከልማቱ ማንም ወደ ኋላ ሳይቀር ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቻልንበት፣የከተማችንን ደረጃ መሻሻል እና የተወዳዳሪነት አቅም የፈጠርንበት፣የሥራ ባህል መሻሻል 24/7፣ የይቻላል አስተሳሰብን ያዳበርንበት፣ የከተማችንን ገጽታ መቀየር/ ለሀገር ክብር አስተዋፅኦ ያደረግንበት የቻልንበት፣ የፕሮጀክት አመራርና የኮንትራት አስተዳደር አቅም ያሳደግንበት፣ የባለድርሻ አካላት አቅም እየጎለበተ የመጣበት ፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት የቅንጀት እና ትብብር ደረጃ በዕጅጉ የተሻሻለበት፣ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረበት ፣በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሰፊ የገበያ ትስስር በመፍጠር ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ለበርካታ ዜጎችን ፍትሐዊነት፣ተጠቃሚነት ያረጋገጥንበት ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት አቅም መጠናከር ሽግግር የፈጠርንበት እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ የቻልንባቸው ውጤታማ ስራዎች ናቸው፡፡

👉በኮሪደር ልማቱ ሥራ ውስጥ የከፍተኛ አመራሩ ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ለተግባራዊነቱ በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በጥብቅ ዲስፕሊን እና መሰጠት ክትትልና ድጋፍ የደረገበት አግባብ፤ ወደ ታች ወርዶ በፕሮጀክት ሳይት ፈጣን ዉሳኔ አየሰጠ መሄድ፣ ሰዉ ተኮር የሆኑ የልማት ተነሺዎች አያያዝና መስተንግዶ፣ የተሻለ የመረጃ አያያዝ እና መረጃ መር ውሳኔ መስጠት የተጠናከረ እና ሀገር በጋራ በመገንባት መንፈስ፤ ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እና የተቋማት ቅንጅት እና ትምምን በጥንካሬ የሚታዩና ባህል ማድረግ ታይቷል።

👉እንዲሁም በጎ ፈቃዳቸውን አሳይተው ለተባበሩ የልማት ተነሽዎች፣ ህዝባችን፣ለሀይማኖት ተቋማት፣ ባለሃብቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ኮንትራክተሮችና አማካሪ ድርጅቶች፣ሌት ተቀን እየተረባረቡ ለሚገኙ የከተማችን ሰራተኞችና አመራሮች፣ ማህበራት፣ የጸጥታ አካላትና ሌሎችም ምስጋና አቀርባለሁ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.