ውሃ አቅርቦትን አና የፍሣሽ ሥራዎችን በተመለከተ
የውሃ አቅርቦት ሥራዎችን በተመለከተ ነባር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት እየተከናወነ ሲሆን፣ባሳለፍናቸው 6 ወራት የተሰሩ አዳዲስ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በተመለከተ 15 የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ በቀን 25,000 ሜትር ኪዩብ ውሀ አቅርቦት ተጨምሯል ተጨማሪ ቀሪ 15 ጉድጓድ በቁፈሮ ላይ ይገኛል።
በተጨማሪ በቀን 100,000 ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው በኦሮሚያ ቡሾፍቱ አካባቢ የሚገኘው የጩቋላ ከርሠ ምድር የውሀ ልማት ፕሮጃክት 13 ጉድጓድ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በቀን 80,000 ሜትር ኪዩብ ውሀ ተገኝቷል።
7 ተጨማሪ ጉድጓድ በቁፈሮ ላይ ይገኛል እንዲሁም በቀን 73,000 ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው የገርቢ የውሃ ግድብ ፕሮጀክትን በከተማው በጀት ለመገንባት ወስነን ሂደት ላይ ይገኛል።
መሰረታዊ የአቅርቦት ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ የከርሠ ምድር ውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ጥናት (Comprensive ground water management project) በአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅትእያስጠናን እንገኛለን፡፡
በቀን 30,000 ሜትር ኪዩብ ማጣራት የሚችል የቦሌ አራብሳ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ተጠናቋል በቀን 104,000 ሜትር ኪዩብ ማጣራት የሚችል የምስራቅ ተፋሰስ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ተጀምሯል።
በቀን 20,000 ሜትር ኪዩብ ማጣራት የሚችል የኮዪ ፈጬ 1 እና 2 የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ተጀምሯል፡፡ ለረጅም ዘመናት ብክለትን በማስከተል እና የጤና ጠንቅ በመሆኑ ሲያስቸግሩ የኖሩ የወንዝና ወንዝ ዳርቻ 23.6 ኪ. ሜትር የማጽዳትና የመንከባከብ ስራ ተሰርቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ፍሳሽን ወደ ወንዞች በመልቀቅ ብክለት ማስከተልን የሚከላከል ደንብ በካቢኔዎች ፀድቆ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
