ባለፉት 6 ወራት በስራ ዕድል ፈጠራ የተመዘገቡ ዉጤታማ አፈፃፀሞች ማሳያ፤-
150,000 የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዞ ለ142,908 ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
በዘርፍ ከፋፍለን ስንመለከት 97,126 (68%) የስራ ዕድል የተፈጠረዉ በአገልግሎት ዘርፍ ሲሆን በኢንዱስትሪ ዘርፍ 30,606(21%) የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
በከተማ ግብርና ዘርፍ 15 ሺ112(11%) የስራ ዕድል ተፈጥሯል፤በዚህም የሴቶች ድርሻ 76,107 (53.3%) ነዉ፡፡
በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዋናው የትኩረት ነጥብ የአምራች ኢንዱሰትሪዎችን አቅም ማጎልበትና አምራች ኢንዱስትሪው የሚያነሱትን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን የመፍታት ስራ ተሰርቷል፡፡
ከዚህም አኳያ የመብራት፤የውሀ እና የመንገድ ችግር የነበረባቸውን ኢንዱስትሪዎች በመለየት መብራት 231 ኢንዱስትሪዎች ችግራቸውን መፍታት ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ የካታል ሊዝ አቅርቦት ለ276 ኢንዱስትሪዎች በማቅረብ እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡
184 ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ወደ ውጪ እንዲልኩ በማድረግ 1,671 አምራች ኢንዱስትሪዎች 725,480,810 ቶን ተኪ ምርት በማምረት 490,630,180 ዶላር የውጪ ምንዛሪ ማዳን ችለዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
