+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የመንገድ ማሻሻያ በሚደረግባቸው ቦታዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 21 ቀን 2017 :- በደቡብ፣ በምዕራብና ሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው የውስጠኛው የቀለበት መንገድ ክፍል ላይ ለትራፊክ አደጋ አጋላጭ ተብለው በተለዩ ሦስት ስፍራዎች የመንገድ ማሻሻያ ማድረግ የሚያስችል የባለድርሻ አካላት የመስክ ጉብኝት ተደርጓል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጀመንት ባለስልጣን እና የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ እንዲሁም የደብሊዉ አር. አይ አመራሮችና ባለሙያዎች በመስክ ምልከታው ላይ ተካፍለዋል።

የመስክ ምልከታ የተደረገው ለትራፊክ አደጋ የሚያጋልጡ እና ለፍሰትም አሉታዊ ተጽኖ የሚያስድሩ ተብለው በተለዩት ሀና ማርያም፣ ጀሞ ሚካኤል እና ዊንጌት አካባቢ ባሉ የውስጠኛው የቀለበት መንገድ ክፍሎች ላይ ነው።

በተቋማቱ በተደረገ ጥናትእና ከህብረተሰቡ በተሰጡ ጥቆማዎች መሠረት የሚካሄደው ይህ የመንገድ ማሻሻያ ሥራ፤ የእግረኛ ማቋረጫ፣ በአንድ አቅጣጫ የተሽከርካሪ መተላለፊያ መስመር የመክፈት እና በመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ የትራፊክ መብራት ተከላን የሚያካትት ነው።

የትራፊክ አደጋን ለመከላከል እና የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ ፤ በተጠቀሱት አካባቢዎች በሚከናወኑ የመንገድ ማሻሻያ ሥራዎች ባለድርሻ አካላት በሚኖራቸው ሚና እና ቅንጅታዊ ሥራዎች ላይ ሀሳብ በመለወጥ ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.