ለሰው ሀብት ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከታህሣስ 14 እስከ 18 ቀን 2017 ድረስ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ሀብት የስራ አፈፃፀም ማኔጅመንት ቡድን መሪ ወ/ሮ ፈቲሃ መሐመድ፤ ሥልጠናው የሰው ሀብት አስተዳደር ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ይበልጥ ለማጎልበት፤ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም የስራ ላይ ሥነ-ምግባር በመላበስ ሠራተኞች የላቀ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ ፈቲሃ አያይዘውም የሰራተኞችን አቅም ለመገንባት መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው፤ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ የተገልጋዮችን እርካታ የሚጨምር አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሥልጠናው ተሣታፊዎች በበኩላቸው፤ በስልጠናው የገበዩት እውቀት በዘርፉ ለሚሰጡት አገልግሎት መሻሻል ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን ጠቁመው፣ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
ስልጠናው በሰው ሀብት አስተዳደር ዙሪያ ለ5 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ 41 የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ሀብትና የሥልጠና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይም ለስልጠናው ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ