በኮሪደር ልማት የተሰሩ መንገዶች የትራንሰፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ የትራፊክ አደጋን መከከላከል አሰችሏል
(ኢ ፕ ድ)
በከተማዋ የተሰራው የመንገድ ኮሪደር ልማት የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥና አደጋን ከመከከላከል አንጻር መሰረታዊ ለውጥ ያመጣ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ በትራፊክ አደጋ ባለፉት ሶስት ወራት 107 ሰዎች ህይወትም አልፏል። ከ900 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና የህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ በከተማዋ የነበሩ መንገዶች በይዘትም በጥራም ከተማዋን የማይመጥኑ ብሎም ለእግረኛ ሆነ ለተሸከርካሪ ምቹ አልነበሩም።
አሁን እየተሰሩ ያሉና የተሰሩ የመንገድ ኮሪደሮች የእግረኛና ተሸከርካሪ መንገድ የለዩ፣ ተሸከርካሪ ፕርኪንግ ቦታዎችን ያስቀመጡና የብስክሌት መንገዶችን ያካተቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህም ከከተማው ገጽታ ግንባታ ባሻገር የመንገድ ትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥና አደጋን ከመከከላከል አንጻር መሰርታዊ ለውጥ ያመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለዚህም የመንገድ ኮሪደሩ በተጠናቀቀበት በአራዳ ክፍለከተማ በተለይም ፒያሣ አካባቢ በጥቅምትና ህዳር ወር ምንም አይነት የሞት አደጋ አለመሰከቱና ጤናማ የትራፊክ ፍሰት መኖሩ ለለውጡ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በከተማዋ የትራፊት አደጋ በ2017 በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከዘጠኝ መቶ በላይ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ያደረሰ ብሎም የአንድ መቶ ሰባት ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ መሆኑን ጠቅሰው፤ የትሪፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጠጠር የወጡ ህጎችን አክብሮ በሀላፊነት በመንቀሳቀስ እራስን ከአደጋ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓም