+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በተሰራው የኮሪደር ልማት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነ ተችሏል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተሰራው የኮሪደር ልማት ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮርደር መሰረት ልማት ጥምር ግብረ ሀይል የ5 ወራት የኮርደር መሰረት ልማት እቅድ አፈፃፀም ስራዎችን በግምገማ መድረክ ላይ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደገለጹት፡- በኮሪደር ልማት ስራ ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ያልሆኑ መንገዶች እንደተስተካከሉ በማድረግ እና በተሰሩ አዳዲስ መንገዶችን ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው አዲስ አበባን ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና እንደስሞ አበባ ለማድረግ በኮሪደር ልማቱ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ቀን ከለሊት እጅ ለእጅ በመያያዝ በርካታ ስራውች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ባለፉት በ5 ወራት ጥምር ግብረ ሃይሉ በቅንጅት በሰራው ስራ 266 ድርጅትን እና 19 ሽህ በሚሆኑ ግለሰቦችን ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ የማስተማሪያ ቅጣት በመቅጣት ወደ መንግስት ካዝና ገቢ መድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን፣የፅዳትና አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የትራፊክ መኔጅመንት ባለስልጣን እና የግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገምግመዋል፡፡

Comments are closed.