+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ የአስፋልት ኮንክሪት ማምረቻ ማሽን በስራ ላይ ዋለ

ታህሣስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ ኃይል የሚያከናውነውን የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ የመፈፀም አቅም የሚያሳድግ አዲስ የአስፋልት ኮንክሪት የማምረቻ ማሽን ሥራ ጀመረ፡፡

በጃፖን መንግስት ድጋፍ ከተገኙት የመንገድ ግንባታና ጥገና የማሽነሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የአስፋልት ኮንክሪት ማምረቻ ማሽን በሰዓት 80 ቶን የማምረት አቅም አለው፡፡

አዲሱ የአስፋልት ኮንክሪት ማምረቻ ማሽን ወደ ምርት ተግባር መግባቱ፤ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ቀደም ሲል የነበረውን የአስፋልት ኮንክሪት ማምረት አቅም በ50 በመቶ የሚያሳድግ ነው፡፡

ይህም በመሆኑ፤ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ የሚያጋጥመውን የአስፋልት ምርት አቅርቦት ችግር በማቃለል፣ የመንገድ ግንባታና ጥገና ኘሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.