+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በሕይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሣስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ራስን የማልማት ክህሎትና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተፅዕኖ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለባለስልጣኑ ሴት ሰራተኞች ተሰጠ፡፡

በራስ መተማመን ፣ ራስን በመግለፅ እና በማወቅ ክህሎት እንዲሁም በኤች.አይ.ቪ / ኤድስ ተጽእኖ ላይ ያተኮረ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ከህዳር 30 ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በሁለት ዙር ተከፍሎ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ከ200 በላይ የሚሆኑ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሴት ሰራተኞች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

ሴቶች በስራ ላይም ሆነ በግል ሕይወታቸው የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመሻገር ወደ ስኬት ለሚያደርጉት ጉዞ የሕይወት ክህሎት ሥልጠናው እገዛ እንደሚኖረው የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ መስፍን ከበረ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.