ክፍት የሆኑ የማንሆል ክዳኖች እየተጠገኑ ነው
ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፡-ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአስፋልት መንገድ ጥገና ስራ ጎን ለጎን በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች በመለየት የጥገና ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ከሰሞኑ አስኮ ፣አዲስ ሰፈር፣ ብርጭቆ ኮንደሚኒየም እና ከኮልፌ 18 መዝናኛ በኢትዮ ጠቢብ እስከ ኪዊንስ ሱፐር ማርኬትአካባቢ የሚገኙ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተጎዱና ክፍት የሆኑ የውሃ መፋሰሻ መስመር ክዳኖች ተጠግነዋል፡፡
የጥገና ሰራው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑትን ሙሉ በሙሉ በአዲስ የመተካት እና እድሳት የሚያስፈልጋቸውን ደግሞ መልሶ በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡
በቀጣይም ክፍት የሆኑ እና በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች የመጠገንና የመቀየር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የማንሆል ክዳን የድሬኔጅ መስመሮች የዝናብ ውሃን በአግባቡ እንዲያስተናግዱ እና የመዲናዋ ጎዳናዎች ውብና ጽዱ ሆነው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል በመሆኑ ሕብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆነውን መንገድ እና የመንገድ አካላትን በባለቤትነት ስሜት ከጉዳት እንዲጠብቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ