+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በዛሬው የምክር ቤታችን ውሎ ለ2017 በጀት ዓመት 230.39 ቢሊዮን ብር በጀት አውጀናል።

ከዚህ ውስጥ 146.48 ቢሊዮን ብር (63.6%) ለካፒታል የተመደበ ሲሆን፣ 74.55 ቢሊዮን ብር (33.4%) ለመደበኛ ወይም ለአስተዳደርዊ ወጪ የተመደበ ነው።

ለካፒታል ከተመደበው ውስጥ 90.4 % ለድህነት ቅነሳ እና እድገት ተኮር ዘላቂ ልማት ለሆኑ ፕሮጀክቶች የተመደበ ነው።

ውድ የከተማችን ግብር ከፋዮች፤ ይህን በጀት ማሳካት የጋራ ርብርብ ይጠይቃል። በ2016 በጀት ዓመት ግብራችሁን በወቅቱ በፈቃደኝነት በመክፈላችሁ 146.8 ቢሊዮን ብር ግብር ሰብስበን 18,091 ፕሮጀክቶችን እና የኮሪደር ልማትን ተግብረን ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ አበባ በማድረግ የጋራ አሻራችንን እያስቀመጥን ነው።

በዚህ ዓመትም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበለጠ ለመስራት ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.