+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በ2016 አፈፃፀምና የ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ተወያይተው የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

አጠቃላይ ከሰራተኞች ለቀርቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረክ ማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ በአዲሱ በጀት ዓመት ስኬታማ ስራዎችን ለማከናወን በተያዘው የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ኢንጂነር ሙህዲን አያይዘውም በ2016 በጀት ዓመት የተገኙ ስኬቶችና መልካም ተሞክሮችን እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ በቀጣይ 2017 በጀት ዓመትም አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የባለስልጣኑ የተቋም ለውጥ እና ድጋፍ ሠጪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ዶሌቦ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ራሷን ለመለወጥ ለምታደርገው ከፍተኛ ጥረት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ከፍተኛውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ፀጋዬ ቦርሴ በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት በከተማዋ የሚገነቡ መንገዶች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከመንገድ ሀብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አወል ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኞች የከተማው መንገድን በመጠበቅና በመንከባከብ አምባሳደር ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 በጀት ዓመት የተገኘውን የመንገድ መሰረተ ልማት ስኬት አጠናክሮ በማስቀጠል፤ በ2017 በጀት ዓመትም ተመሳሳይ ድሎችን ለመድገም ሁሉም አመራርና ሠራተኞች በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.