የመሬት እና መሬት ነክ አፈፃፀም በተመለከተ:-
በበጀት ዓመቱ 1,504.27 ሄክታር መሬት ለተለያዩ የልማት ሥራዎች በማዘጋጀት 859.47 ሄ/ር መሬት በውሳኔና በጨረታ ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
የተለያዩ ፕሮጀክት ማለትም የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የልማት ተነሺዎች 6.2 ቢሊየን ብር ካሳ መክፍል የተቻለ ሲሆን በፕሮጀክቱ ለሚነሱ የልማት ተነሺዎች እጅግ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለ2,538 ቦታዎች (33.4 ሄ/ር) ምትክ መሬት ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
የመሬት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እንዲሁም ከሌብነት እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተቀናጀ የመሬት አስተዳደር መረጃ ሥርዓት (integrated land management system) ተግባራዊ በማድረግ 723,101 ማኅደሮች በማጥራት ስካን ተደርገው ዘመናዊ የመረጃ ቋት ውስጥ በማስገባት 40 የመሬት አገልግሎቶች ኦንላይን እንዲሰጡ ተደርጓል።
128,401 ቁራሽ መሬትና ኮንዶሚኒየም ቤቶች በፓርሴል ለማረጋገጥ ታቅዶ 179,512 ከእቅድ በላይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ለ73,109 ይዞታዎች የምዝገባ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡
አገልግሎት የተሰጠባቸው ማህደራት ላይ የሕግና የቴክኒክ አሰራር ኦዲት ተደርጎ በግኝቶቹ ላይ ማስተካኪያ እርምጃ ተወስዷል።
በበጀት ዓመቱ የመዋቅራዊ ፕላን አካል የሆነውና የከተማችንን ገጽታ የሚቀይር፣ በተለያዩ ጊዜያት የለሙ ሥራዎችን ሊያያይዝ የሚችልና፣ አጠቃላይ የከተማዋን እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ 1,435.6 ሄ.ር. የሚሸፍኑ የኮሪደር ልማት ፕላን እንዲሁም 1,365 ሄ.ር. የሚሸፍኑ 13 የአካባቢ ልማት ፕላኖች ፀድቀው ተግባራዊ ተደርገዋል፡