+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የናሳው ሪልስቴት- አርሴማ ቀለበት መንገድ ግንባታ አሁናዊ ገፅታ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 25 ቀን 2016 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ አቅም እየገነባቸው ከሚገኙ አቋራጭ መንገዶች መካከል የሆነው የናሳው ሪልእስቴት – አርሴማ ቀለበት መንገድ መጋጠሚያ አንዱ ነው፡፡

ይህ መንገድ በአጠቃላይ 1.28 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን የትራፍክ ፍሰት በማቀላጠፍ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ርዝመት ውስጥ 1 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር የሚሆነው አስፋልት የለበሰ ሲሆን፣ ቀሪ የእግረኛ መንገድ ታይልስ ንጣፍ እና ተያያዥ ስራዎችን ለማጠናቀቀ በቀጣይ የሚሰራ ይሆናል፡፡

አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ፊዚካል አፈፃፀም 86 በመቶ ደርሷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.