የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ብልሽት የገጠማቸውን የድሬኔጅ መስመሮች በማፅዳትና በመጠገን ላይ ነው።
የከተማዋ የመንገድ ዳር ውሃ መፋሰሻ መስመሮች እየገጠማቸው ባለው ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀምና እንክብካቤ ጉድልት ምክንያት በተደጋጋሚ በደረቅ ቆሻሻ የተደፈኑ አገልግሎታቸው እየተስተጓጎለ ይገኛል፡፡
በሰኔ ወር የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል፤ ከሰሜን ማዘጋጃ – አዲሱ ገበያ፣ ጀሞ 1 የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ከሲ.ኤም.ሲ – ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ – አቤም ሆቴል አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ባለሥልጣን መስሪያቤቱ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ብቻ ከ375 ኪሎ ሜትር በላይ ርቅት የሚሸፍን የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ሥራዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፤ በቀጣይ የክረምቱ ወራትም ይህንኑ ተግባር ከሌሎች የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ጎን ለጎን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ሕብረተሰቡም የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱን በማዘመን የጋራ መጠቀሚያ የሆነውን የመንገድ ሀብት በባለቤትነት ስሜት ከጉዳት እንዲጠብቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዘወትር መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369