+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የድል በር – ኬላ መንገድ ጥገና በተጠቃሚዎች ዕይታ

ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ አካባቢዎች ከሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ የመንገድ ግንባታ ሥራዎች ጎን ለጎን፤ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ መንገዶችን በመጠገን ምቹ ለትራፊክ እንቅስቃሴ እየፈጠረ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ጥገና ካደረገላቸው ዋና ዋና መንገዶች መካከል ከድል በር ወደ ኬላ የሚወስደው የከተማዋ ሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የመውጫና መግቢያ ኮሪደር ይገኝበታል፡፡

ከመዲናዋ አምስት የመግቢያና መውጫ በሮች መካከል አንዱ የሆነው ይህ መንገድ፤ በየዕለቱ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግድ እና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጠ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ችግሩን ለመፍታት በበጋው ወራት መጀመሪያ ላይ ከድል በር እስከ እንጦጦ ኬላ የሚሸፍን ሰፊ የመንገድ ጥገና ሥራ አከናውኗል፡፡

በበጀት ዓመቱ በመልሶ ማልማት ደረጃ ጥገና የተደረገለት ይህ መንገድ፤ በትራፊክ እንቅስቃሴው ላይ ያመጣውን ለውጥ ለመዳሰስ የመንገዱን ተጠቃሚዎች አነጋገረናል፡፡

በአካባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ሚኪያስ ተፈራ፤ ቀደም ሲል መንገዱ በከፍተኛ ሁኔታ በመቦርቦሩ ምክንያት ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ ከመሆኑም ባሻገር በተሽከርካሪዎች ላይም ጉዳት ይደርስ እንደነበር ጠቅሰው፤ አሁን ላይ መንገዱ በዚህ ደረጃ ተሻሽሎ መጠገኑ ቀልጣፋ እንቅስቃሴ እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ በጉዞ ላይ ይባክን የነበረውን ጊዜ ማሳጠሩን ተናግረዋል፡፡

ሌላው በአካባቢው በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩት አቶ አማኑኤል በበኩላቸው፤ መንገዱ ወደ ሰሜን ሸዋ፣ ጎጃምና ጎንደር የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ጭምር የሚተላለፉበት ዋና መንገድ በመሆኑ ከፍተኛ የትራፊክ ጫና ያለበት መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ መንገዱ በመጠገኑ ለስራቸው ምቹ እንደሆነ እና መንገዱም የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የእርስዎን ሃሳብና አስተያየት በ comment ላይ ያጋሩን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.