በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ቀን 2016ዓ.ም፡- ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለስልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞች ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወይዘሪት ፀደንያ አበበ እንደገለፁት የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ስርጭት አሁንም በሀገራችን እንዳለ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ጠቁመው፤ በበሽታው ስርጭት ላይ የሚታየውን መዘናጋት ለመቀነስ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ማስፈለጉን ገልፀዋል፡፡
ወይዘሪት ፀደንያ አያይዘውም በህብረተሰቡ ዘንድ በሽታው ጠፍቷል የሚል የተሳሳተ እሳቤ በመኖሩ ለቫይረሱ የሚሰጠው ጥንቃቄና ትኩረት በመቀነሱ ምክንያት አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል እያጠቃ መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ስንታየሁ ጎሹ እንዳሉት ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የህብረተሰቡን ግንዛቤ በየጊዜው ማዳበር እንደሚያስፈግ ገልፀዋል፡፡
የሀገራችንን የኤች.አይቪ/ኤድስ ስርጭት ነባራዊ ሁኔታ ፣ የመከላከያና መተላለፊያ መንገዶች እንዲሁም የህይወት ክህሎት ላይ በማተኮር የተሰጠው ስልጠና ሰራተኞች ያላቸውን ክህሎት ለማሳደግ እና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት በተሻለ ተሳትፎ ለማገዝ የሚያስችል መሆኑን አቶ ስንታየሁ ነግረውናል ፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው በማጋራ በሀገራችን ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሳቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡
በ5 ዙር ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው ስልጠና 500 የሚሆኑ የባለስልጣኑ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369