+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከ52 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት የሚሸፍን የኮብል መንገዶች ጥገና ሥራ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች 52.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የውስጥ ለውስጥ የኮብል መንገዶች ጥገና ስራ ለማስጀመር ዝግጅት አጠናቋል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ከሚያከናውነው የአስፋልት መንገዶች ግንባታ ጎን ለጎን፤ የተጎዱ የኮብል መንገዶችን በመጠገን የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ እየሰራ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተመረጡ 60 ማህበራትን በማሳተፍ የኮብል መንገዶች ጥገና ለማስጀመር የሳይት ርክክብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከማህበራት ጋር የሳይት ርክክብ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6፣ በተለምዶ ባሌስትራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 450 ሜትር ርቀት የሚሸፍን የውስጥ ለውስጥ የኮብል መንገድ ጥገና ስራ ይገኝበታል፡፡

Comments are closed.