የመንገድ መብራት አስተዳደር ደንብ
ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የመንገድ መብራት አስተዳደር ደንብን አፅድቋል፡፡
ቀደም ሲል በከተማዋ በዋና ዋና እና መጋቢ መንገዶች የተተከሉ የመንገድ ዳር መብራቶችን ጥገና እና የማሻሻያ ሥራ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በኩል ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።
አሁን ላይ አዲስ አበባ የደረሰችበትን አጠቃላይ የእድገት ደረጃ እና የወደፊት ትልሟን ታሳቢ በማድረግ፣ በላቀ ደረጃና በተሟላ መልኩ የመንገድ መብራት አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ፤ ከዚህ የሚከተለው ደንብ በከተማው አስተዳደር ካቢኔ ፀድቋል።
ዝርዝሩን እንደሚከተለው አቅርበናል፦