+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቦሌ ቡልቡላ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽ ለማድረግ በርካታ የመንገድ ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው በ390 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12 በሚገኘው ቡልቡላ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ የሚጠቀስ ነው፡፡

የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው ሶፍ ዑመር ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን.፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ጎጎት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ይከታተለዋል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ 1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትሩ በአስፋልት እንዲሁም ቀሪው 1ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል ደግሞ በኮብል ደረጃ የሚገነባ ነው፡፡

የመንገድ ግንባታው የአካባቢውን ነዋሪዎች የመውጫ እና የመግቢያ የመንገድ ችግር ከመቅረፉም በተጨማሪ፣ ከቦሌ ቡልቡላ ወደ ሳሪስ አቦ ከሚወስደው መንገድ ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ የትራፊክ ፍሰትቱን የተሳለጠ በማድረግ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት እንደሚያፋጥን ይታመናል፡፡

በመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ ክልል እስካሁን ድረስ ያልተጠናቀቁ የወሰን መስከበር ሥራዎች መኖራቸው በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ።

በመሆኑም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፈጣን ምላሽ በመስጠት ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ባለስልጠን መስሪያቤቱ በጀት ዓመቱ በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት በ40/60 እና በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከ22 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን በአስፋልት እና በኮብል ንጣፍ መንገድ በተለያዩ የስራ ተቋራጮች እያስገነባ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

Comments are closed.