+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የመንገድ ዳር መብራት ማሻሻያ ስራዎች

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት አስር ወራት በተለያየ ምክንያት ለብልሽት የተጋለጡ የመንገድ መብራቶችን በመጠገንና ደረጃቸውን በማሻሻል ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት 16 ሺህ የሚደርሱ የከተማዋን የመንገድ ዳር መብራቶች ለመጠገን አቅዶ፤ ባለፉት 10 ወራት ብቻ ከ61 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ11 ሺህ 6 መቶ በላይ የመንገድ መብራት ምሶሶዎችን በመጠገን እና ከ6 ሺህ በላይ ኤል. ኢ. ዲ አምፖሎችን በመቀየር ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡

በከተማዋ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ስርቆትና የተሸከርካሪ ግጭት ለአገልግሎት መቆራረጥ ዋነኛ መንስኤ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡

በመሆኑም ከፍተኛ የህዝብና የመንግስት ሃብት ፈሶባቸው የተዘረጉት የመንገድ ዳር መብራቶች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይችሉ ዘንድ ሕብረተሰቡ ከጉዳት እንዲጠብቃቸውና እንዲንከባከባቸው ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.