የተቋሙ የግንባታ ግብዓት ማምረቻዎች
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ አቅም የሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የአፈፃፀም ደረጃቸውም ከጊዜና ጥራት አኳያ ሲመዘን እድገት እያስመዘገበ መጥቷል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በመንገድ ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽና ውጤታማ ለማድረግ ቁልፍ ድርሻ ያላቸውን የሰው ኃይሉን፣ የግንባታ መሣሪያዎችና ግብዓቶችን ከመጠነ ሰፊ ዕቅዶቹ ጋር በማጣጣም ለማሳካት በከፍተኛ ትጋት እየተረባረበ ይገኛል፡፡
በዚህ ፅሁፍ ከፍ ብለው ከተጠቀሱት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የስልተ-ምርት መስተጋብሮች አንዱ በሆነው የግንባታ ግብዓት ማምረቻዎች ላይ ትኩረት አድርገን ተቋማዊ መረጃዎችን በአጭሩ እንካፍላችኋለን፡-
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ከፍተኛ መጠን ያላቸው ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ጥቅም ላይ ያውላል፡፡
ከእነዚህም መካከል ገረጋንቲ፣ ሰብ ቤዝ፣ ቤዝ ኮርስ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የጠጠር ምርቶች፣ ነጭ ድንጋይ፣ ቀይ አሸዋ፣ አስፋልት ባይንደር እና ዊሪንግ፣ ፕራይም ኮት እና ልዩ ልዩ የስሚንቶ ውጤቶች ይገኙበታል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ኃይል ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች አገልግሎት ከ80 እስከ 85 በመቶ የሚሆነውን የግንባታ ግብዓት ፍላጎት የሚያሟላው፤ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ውስጥ ካደራጃቸው 11 የግብዓት ማምረቻ ስፍራዎች በሚመረቱ ልዩ ልዩ የግንባታ ምርቶች ነው፡፡
በየዓመቱ ከ800 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓት ምርቶች የሚያመርቱት የሥራ ክፍሎች በቦሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ከ980 በላይ ቋሚና ጊዜያዊ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች በግብዓት ምርት ሥራው ላይ ይሳተፉበታል፡፡
ለውድ የገፃችን ተከታዮች መልካም የሥራ ሣምንት መጨረሻ፣
የእረፍት ቀናትን እና የምሽቱን ክፍለ ጊዜ ጭምር በሥራ ላይ ለሚያሳልፉ ባልደረቦቻችን ደግሞ መልካም የሥራ ጊዜን እንመኛለን!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ ገፃችንን ይጎብኙ :- http://www.aacra.gov.et