+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለሥልጣን መስሪያቤቱን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም የሚቃኝ ሱፐርቪዥን እየተካሄደ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ድጋፍና ክትትል በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የሱፐርቪዥንና የመስክ ጉብኝት መርሃ ግብሩ ከግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም የጀመሮ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣ እስከ ግንቦት 13 ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

መርሃ ግብሩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የቢሮ አደረጃጀትና የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የግንባታ ግብአት ማምረቻ ሳይቶችን ጨምሮ የተመረጡ የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴዎችን በመቃኘት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በእስከ አሁኑ ሂደት የባለሥልጣን መስሪያቤቱን አደረጃጀትና አገልግሎት አሰጣጥ የተመለከቱ ሲሆን፣ በተጨማሪም የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በመስክ ተገኝተው ተመልክተዋል።

በቀሪዎቹ ቀናትም የቋሚ ኮሚቴው ተጨማሪ የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና የባለስልጣን መስሪያቤቱን የ9 ወራት አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም በመመልከት ግብረ-መልስ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.