የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል ማዕድ የማጋራት መርሃ-ግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በሚገኘው ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በጎዳና ላይ ለሚገኙና ለአቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝና የዛሬው የአቅመ ደካሞች የበዓል ምገባ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዜጎች ያላቸውን በማጋራትና በማብላት በዓሉን በደስታና በፍቅር ሊያሳልፉት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369