ከሳዕሊተ-ምህረት ወደ አያት 49 በሚወስደው ጎዳና ላይ የእግረኛ መንገድ መልሶ ግንባታ እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች የእግረኛ መንገድ ግንባታ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በነባር መንገዶች ላይ የእግረኛ መንገድ ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከሳዕሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን – በፊጋ – ሰሚት 72 – አያት 49 ድረስ የሚያገናኘው መንገድ ይጠቀሳል፡፡
አሁን ላይ በተለያየ ምክንያት ለብልሽት የተዳረገውን ነባሩን የእግረኛ መንገድ ሙሉ በሙሉ በማንሳት፣ በመልሶ ግንባታ ደረጃ የእግረኛ መንገድ ግንባታ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በመልሶ ግንባታ ደረጃ እየተገነባ የሚገኘው ይህ የእግረኛ መንገድ በአጠቃላይ 10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን እና 4 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ ግንባታው በስድስት የጥቃቅንና አነስተኛ ተመራቂ ማህበራት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት እየተገነቡ የሚገኙት የእግረኛ መንገዶች የትራፊክ አደጋን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ አዲስ አበባን ውብ ገፅታ እያላበሷት ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369