+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የኮሪደርና የመልሶ ማልማቱ ፋይዳዎች

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የከተማዋን የልማት ኮሪደር ስራዎች መተግበት የሚያስገኛቸውን ፋይዳዎች በማስመልከት ከተናገሩት:-

👉የኮሪደርና የመልሶ ማልማቱ ለከተማችን ነዋሪዎች ካስገኛቸዉ ፋይዳዎች መካከል በልማቱ ምክንያት ተነሺ የሆኑ እጅግ በጎሰቆሉና ለመኖር በማይመቹ ቤቶች፣ በተደጋጋሚ የእሳትና የጎርፍ አደጋ እንዲሁም ለብክለት ሲዳርጉ የነበሩ የመሰረተ ልማት ጉድለቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ሲኖሩ የነበሩ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ቤት አግኝተዋል፡፡

👉የከተማ ኘላን በተለይም ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ (ድሬኔጅና ስዌሬጅ) የቴሌኮም፣ የመብራት፣ የደህንነት መጠበቂያ ካሜራዎች በተቀናጀ መንገድ በመሬት ውስጥ እየተሰሩ በመሆኑ የከተማ ስርዓትን በልኩ የሚያሳልጥ ይሆናል፡፡

👉ለከተማችን ነዋሪዎች ውብና ማራኪ የአረንጓዴ እና ሰፋፊ የህዝብ የጋራ መገልገያዎች፣ መዝናኛ ቦታዎች እና የህፃናት መጫወቻዎች የከተማችንን ገፅታ የሚያሻሽሉ ሲሆን የትራፊክ ፍሰቱንና የትራንስፖርት ችግርንም የሚያቃልሉ የአውቶቢስና ታክሲ ተርሚናሎች፣ የምድር ዉስጥ ፓርኪንግ፣ ምቹ የታክሲ ማውረጃና መጫኛ ተርሚናሎች፣ የመሮጫ ትራኮች፣ የእግረኛ መንገዶች ፣ የሳይክል መንገድ፣ የእግረኛ መሿለኪያና መሸጋገሪያ ድልድዮች እንዲሁኝ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሻሽሉ ስራዎችም ተካተውበታል::

👉ከስራ እድል አንፃር በኮሪደር ልማቱና በመልሶ ማልማት እንዲሁም በአረንጓዴና ከተማ ውበት ዘርፎች በአጠቃላይ በቋሚነት ለ1,485 እና በጊዜያዊነት ለ13,784 በድምሩ ለ15,269 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡

👉ከተማችን አህጉር-አቀፍና አለም-አቀፍ ሚናዋን እንድትወጣ እና ተወዳዳሪ እንድትሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

👉የኮሪደር ልማቱ በተሟላ ሁኔታ ሲጠናቀቅ በነዚህ ቦታዎች ከመልሶ ማልማት በፊት ተፈጥሮ የነበረውን የስራ እድል በ51% ያሳድጋል ፣ የከተማዋን ገቢና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ይጨምራል እንዲሁም ከተማዋን የስማርት ሲቲ አገልግሎት አሰጣጥን ለመተግበር መሰረት ይጥላል፡፡

Comments are closed.