+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የፈረንሳይ ፓርክ- አቦ ቤተክርስቲያን የመንገድ ግንባታ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ኃይል ከሚገነባቸው መንገዶች መካከል አንዱ የሆነውን የፈረንሳይ ፓርክ- አቦ ቤተክርስቲያን የመንገድ ግንባታ የአስፋት ማንጠፍ ስራው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

የፈረንሳይ ፓርክ -አቦ ቤተክርስቲያን የአስፋልት መንገድ ከመገንባቱ በፊት በአካባቢው ምንም አይነት የመንገድ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች ለረጅም ጊዜያት የቆየ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄ እንደነበራቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ የህብረተሰቡን የመንገድ መሰረተ-ልማት ፍላጎት ለማሟላት በአጠቃላይ 1.2 ኪሎ ሜትር ርዝመትየሚሸፍን እና 15 ሜትር የጎን ስፋት ያለው የአስፋልት መንገድ ገንብቶ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ አካል የሆነው የእግረኛ መንገድ ታይልስ ንጣፍ፣ የመንገድ ዳር መብራት ተከላ፣ የድጋፍ ግንብ ስራና ተያያዥ ቀሪስራዎችን በቀጣይ ጊዜያትለማጠናቀቀ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳደግ ከመሆኑም ባሻገር፣ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ወደ ፈረንሳይ አቦ ቤተክርስቲያን እና አካባቢው ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አቋራጭ መንገድ በመሆን የጉዞ ሰዓት የሚቀንስ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.