የቅየሳ እና የመረጃ አያያዝ አሠራርን የሚያጎለብት በተግባር የተደገፈ ስልጠና እየተሰጠ ነው
መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የቅየሳ ባለሙያዎችን አቅም የሚያሳድግ በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ኃይል የሚያከናውናቸውን የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች የመፈፀም አቅም ለማሳደግ በየጊዜው በተለያዩ መስኮች የሙያተኞች አቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ላይ ሲሆን፣ አሁን ላይ በቅየሳ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሙያተኞች በ Total station እና GPS አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ስልጠና ይገኛል፡፡
ስልጠናውን እየሰጠ የሚገኘው የሰርቬይ ሲስተምስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አሰፋ እንደገለጹት መሣሪያዎቹ ለአጠቃቀም በጣም ቀላልና ዘመናዊ ሶፍትዌር የተገጠመላቸው በመሆናቸው የቅየሳ ስራዎችን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተግባር የተደገፈው ይህ ስልጠና፤ ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ ብዙ ዳታዎችን ለመሰብሰብ የሚያስችል አሰራርን ያካተተ በመሆኑ ለቅየሳ እና ዲዛይን ባለሙያዎች ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity