+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የድልድይ ጥገና እና መልሶ ግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ነው

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በረጅም ጊዜ አገልግሎት እና በአጠቃቀም ጉድለት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ነባር ድልድዮች በጥገና እና በመልሶ ግንባታ ደረጃ እየሰራ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የድልድይ ጥገና ስራ የተከናወነ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል ኮተቤ አማኑኤል ገዳም አካባቢ፣ አቧሬ አካባቢ፣ ፈረንሳይ ድልድይ እንዲሁም አንጀሶ ወንዝ ድልድይ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባለፉት ስምንት ወራት 14 የድልድይና የድጋፍ ግንብ ጥገና ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን፣ በቀጣይም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ድልድዮች በመለየት የጥገና ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ሁሉም የሕብረተሰብ በየአካባቢው የሚገኙ የመንገድ መሰረተ-ልማቶችን በባለቤትነት ስሜት በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በአግባቡ በመጠቀም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.