+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የኤድናሞል -22 ማዞሪያ እንግሊዝ ኤምባሲ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16 ቀን 2016፡- ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ የሚደረግበት የኤድናሞል -22 ማዞሪያ – እንግሊዝ ኤምባሲ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አቅራቢያ የአፈር ቆረጣ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የማንሆል እና የሙሌት ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 4.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 25 ሜትር የጎን ስፋት ይሸፍናል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚችሉና የትራፊክ ፍሰቱን የሚያሻሽሉ ልዩ ልዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የሚያካትት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.