የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሴት ሠራተኞች የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎበኙ
መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሴት ሠራተኞች የጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባውን ሙዚየምን ጎበኙ፡፡
ጉብኝቱ ላይ 110 የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሴት ሰራተኞች የተካፈሉ ሲሆን፣ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የአድዋ ድል መታሰቢያ ማዕከሉ የአሁኑ እና መጪው ትውልድ የጋራ ታሪኩን እንዲያውቅና በየዘመኑም አዳዲስ አንፀባራቂ ድሎችን በአብሮነት እንዲያስመዘግብ ከፍተኛ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአድዋ ድል፤ ፍቅርን፣ መተማመንና በጋራ መቆምን የሚያስተምር መሆኑን የገለፁት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች፤ በአድዋው ጦርነት ወቅት ሴቶች ዘማቾችን ከማበረታታትና ስንቅ ከማቀበል ባለፈ እንደ ጦር መሪ ቁልፍ የሆኑ ስልቶችን በመጠቆም ለድሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበረከታቸውን መገንዘባቸውን ገልፀዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የአድዋ ዘመን ጀግኖች ሴቶችን አኩሪ ገድል እና አርዓያነት ያለውን ተግባር አብነት በማድረግ፣ ዛሬም እንደ ትናንቱ የዚህን ዘመን መልካም ታሪክ ለማኖር በተሰለፉበት የሥራ መስክ ተግተው በመስራት የበኩላቸውን አሻራ እንደሚያኖሩ አረጋግጠዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity