+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቦሌ ቡልቡላ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12 በሚገኘው ቡልቡላ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የመንገዱን ግንባታ እያከናወነው የሚገኘው ሶፍ ዑመር ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን.፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ጎጎት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ይከታተለዋል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ 1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትሩ በአስፋልት እንዲሁም ቀሪው 1ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል ደግሞ በኮብል ደረጃ የሚገነባ ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 390 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ሲሆን፣ አሁን ላይ የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የቱቦ ቀበራ እና ተያያዥ ስራዎች በመከናነወን ላይ ናቸው፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.