+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከኪዳነምህረት አደባባይ ወደ መንዲዳ የሚወስደው መንገድ ጥገና እየተደረገለት ነው

መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከኪዳነ ምህረት አደባባይ ወደ መንዲዳ የሚወስደውን መንገድ በመጠገን ላይ ይገኛል።

የጥገና ስራው የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት እየተከናወነ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው።

የመንገዱ መጠገን ከአየርጤና – ኪዳነምህረት አደባባይ – የሺደበሌ አደባባይ – ጦርኃይሎች እንዲሁም ቀራንዮ ያለውን የትራፊክ እንቅስቃሴ የተሳለጠ ያደርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.