የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም – ውጭ ቀለበት የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በስራ ተቋራጮች እያስገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም – የውጨኛው ቀለበት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 1.4 ኪ.ሜ ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ አሁን ላይ የአስፋልት ማንጠፍ፣ የእግረኛ፣ የመንገድ ዳር መብራት ፖል ተከላ እና የቀለም ቅብ ስራዎች ተጠናቀው የትራፊክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የግንባታ ስራውን ዲሪባ ደፈረሻ በተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ ከ185.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት የተከናወነ ሲሆን የማማከርና የግንባታ ቁጥጥር ስራውን ደግሞ ጎንድዋና አማካሪ ድርጀት ሲከታተለው ቆይቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity