ከጀሞ አፍሪካ ሕንፃ -ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ የመንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ኃይል እየገነባው የሚገኘው የጀሞ አፍሪካ ሕንፃ -ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ የመንገድ ግንባታ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ተሸጋግሯል፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የመንገድ ዳር መብራት ተከላ እና የእግረኛ መንገድ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት የመንገድ ፕሮጀክቱ የፊዚካል አፈፃፀም ከ90 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ቀሪ የተደራቢ አስፋልት፣ የእግረኛ መንገድ፣ የቀለም ቅብ እና የመንገድ ዳር መብራት ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ በዚህ በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት ይደረጋል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከጀሞ ሚካኤል የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ወደ ጀሞ ትራፊክ መብራት እና አካባቢው ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡