የባለስልጣኑ ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30 ቀን 2016ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በትናትናው ዕለት አክብረዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ በንግግራቸው፤ በሀገራችን ግማሹን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች በመሆናቸው በተለያዩ የስራ መስኮች በማሳተፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ለባለስልጣን መሥሪያቤቱ ሴት ሰራተኞች የስራ ክህሎት ስልጠና በመስጠት፣ የትምህርት እድል በማመቻቸት ሴት አመራሮችን በማበረታታት ተቋሙ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው፤የሴቶችን ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም ማህበራዊ ጫና መከላከል የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሴቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወ/ሪት ፀደንያ አበበ በበኩላቸው ሴቶችን እናብቃ ሲባል የሴቶችን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማክበር ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ቀኑን የተመለከተ የመወያያ ሰነድ እና የማህፀን በር ካንሰር ምንነት በተመለከተ ለዝግጅት ታዳሚዎች ገለፃ ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም በተያዘው በጀት ዓመት የአገልግሎት ጊዜያቸው አጠናቀው በጡረታ ለተገለሉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴት ሰራተኞች የምስጋናና እውቅና የመስጠት መርሀ-ግብር ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity