+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከሾላ ገበያ ወደ ሃያ ሁለት የሚወስድ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ መረብ ይበልጥ ለማስተሳሰርና የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል ከሚያከናውናቸው የዋና ዋና መንገዶች ግንባታ በተጨማሪ የመጋቢ መንገዶች ግንባታም እያከናወነ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል በየካ ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ 11 ሃያ ሁለት አካባቢ ከኬብሮም ፋርማሲ ወደ ዮናስ ሆቴል የሚወስደው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ይገኝበታል፡፡

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በራስ አቅም እየገነባው ያለው ይህ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እግረኛና የአስፋልት መንገዱን ጨምሮ በአጠቃላይ 530 ሜትር ርዝመት እና 15 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡

አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ ፣ የቱቦ ቀበራ እና ተያያዥ ስራዎች በመከናነወን ላይ ናቸው፡፡

የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከሾላ ወደ ሃያ ሁለት እና ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አማራጭ መጋቢ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.