ለስልጠና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ያዘጋጀውን የአገልጋይነትና የክህሎት ብቃት ስልጠና በማሰልጠን በስኬት ላጠናቀቁ 25 የባለሥልጣኑ ሠራተኞች የዕውቅና ሠርትፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
እነዚህ ባለሙያዎች 1 ሺ 261 ለሚሆኑ የተቋሙ ሠራተኞች በስነምግባር፣ በተግባቦት ክህሎት፣ በስሜታዊ ልህቀት እና በደንበኞች አገልግሎት ዙሪያ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ውጤታማ ስልጠና መስጠታቸውን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ከበረ ገልፀዋል፡፡
አቶ መስፍን አክለውም ስልጠናውን የወሰዱት የባለሥልጣኑ ሠራተኞችም የመፈፀም አቅማቸውን ለማጎልበት እንደረዳቸው ባደረግነው የዳሰሳ ጥናት ለማረጋገጥ ችለናል ብለዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ስልጠናውን ሲሰጡ ለቆዩ የመጀመሪያ ዙር አሰልጣኞች በበኩላቸው፤ በአሠልጣኝነት ለተሳተፉ ሙያተኞች እውቅና መስጠቱ፣ በቀጣይም በራስ አቅም እና በአነስተኛ ወጪ ውጤታማ ስራ ለመስራት እንደሚያግዛቸው ያነጋገርናቸው የስልጠና ባለሙዎች ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity