አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ቀን 2016ዓ.ም፡-
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ቀን 2016ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንደሰርድን የሚያሟሉ አዳዲስ አራት የመንገድ ኮሪደሮች ግንባታ እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኙትን ሁለት የእግኛ መሸጋገሪያ የብረት ድልድዮች የማንሳት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
“አራት ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ የሚገኘው የእግረኞች መሸጋገሪያ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል” በሚል የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተላለፈው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
የብረት ድልድዮችን የማንሳት ስራ በሁለት ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለስልጣኑ ያስታውቃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity