+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአውጉስታ- ወይራ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በተለምዶ አውግስታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እስከ ወይራ ሰፈር ድረስ ሲገነባ የቆየው የመንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ተጠናቆ የትራፊክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ 1.5 ኪ.ሜ ርዝመት እና 25 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን በከተማዋ እየተገነቡ ከሚገኙ በርካታ አጫጭርና አቋራጭ መንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡

አሁን ላይ የመንገዱ የቀለም ቅብ፣ የእግረኛ መንገድ እና የመንገድ ዳር መብራት ፖል ተከላ ስራዎችም ተጠናቀው ሙሉ በሙሉ የትራፊክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የመንገዱ ግንባታ መጠናቀቅ መቻሉ ከጦር ሀይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው የውጪ ቀለበት መንገዱን በመያዝ በአውግስታ ወደ ቀኝ በመታጠፍ ወይራና ቤተል አደባባይ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች በአቋራጭ እና በአማራጭነት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.