+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ አደባባይ የማሻሻያ ግንባታ ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ተሸጋግሯል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በተለምዶ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአደባባይ ማሻሻያ ግንባታ ከ95 በመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡

አደባባዩ ከጦር ኃይሎች፣ ከብስራተ ገብርኤል እና ከዘነበ ወርቅ አካባቢዎች የሚመጡ ተሸከርካሪዎችን የሚተላለፉበት እና ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግድ በመሆኑ በአካባቢው የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ይከሰት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ላይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀደም ሲል የነበረውን አደባባይ ሙሉ በሙሉ በማንሳት በትራፊክ መብራት ለመቀየር የሚያስችሉ የግንባታ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት የግንባታ ስራው ከ95 በመቶ በላይ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ በቀሪ ውስን ቦታዎች ላይ አስፋልት የማንጠፍና የማስተካከያ ስራዎችን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ በምሽትም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.