ለባለስልጣኑ የጥበቃ ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየው የስራ ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ ጋር በመተባበር 110 ለሚሆኑ የባለሥልጣኑ ጥበቃ ሠራተኞች ለ 6 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በምርቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር መኮነን አሻግሬ እንደገለፁት፤ አካዳሚው ባለፉት 33 ዓመታት በርካታ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አካላት አሰልጥኖ ማስመረቁን አውስተው፤ የረጅም ጊዜ ልምድና ዝና ባለው አካዳሚ ስልጠና ለወሰዱ የባለስልጣኑ የጥበቃ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ሥልጠናቸውን አጠናቀው የተመረቁ የባለሥልጣኑ ጥበቃ ሠራተኞች ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ባሻገር፣ ለከተማዋ ሠላምና ፀጥታ የበኩላቸውን አውንታዊ ድርሻ በማበርከት ተደማሪ አቅም እንደሚሆኑ እምነታቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።
ሥልጠናው በመሠረታዊ የወታደራዊ አቋቋሞ፣ የመሣሪያ አያያዝና አጠቃቀም፣ የፍተሻ ሁኔታዎች፣ ሥነ-ምግባርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተቋም ለውጥና ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ደፋር በበኩላቸው ከተማዋ ፍፁም ሠላም እንድትሆን የፖሊስና የፀጥታ አካላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ ስልጠናውን የወሰዱ የተቋሙ ጥበቃ ሰራተኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ፣ በባስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚገጥሙ የስርቆትና መሰል ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተቋሙ የሚያጋጥሙ ማንኛውም አይነት የደህንነትና የፀጥታ ችግር ለመከላከል ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ባወጡት በለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity