+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በንብረት አያያዝና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ ጋር በመተባበር 110 ለሚሆኑ የባለሥልጣኑ ጥበቃ ሠራተኞች ለ 6 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በባለስልጣኑ የሰው ሀብት የስራ አፈፃፀም ማኔጅመንት ቡድን መሪ ወ/ሮ ፈቲሃ መሐመድ፤ የተቋሙ የጥበቃ ሠራተኞች ካላቸው ክህሎትና ልምድ በተጨማሪ በስነ-ምግባር፣ በንብረት አያያዝ እና በስራ ስምሪት ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እና ለማዳበር የሚያግዝ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሠልጣኞቹ ከየካቲት 18 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት በኮልፌ ፖሊስ አካዳሚ በሚኖራቸው ቆይታ፤ በመንግስት ንብረት ግምጃ ቤቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ስለሚወሰዱ እርምጃዎች፣ በፍተሻ ወቅት ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች፣ ስለንብረት ደህንነትና የጥበቃ፣ ስለ መሰረታዊ ወታደራዊ አቋቋም፣ ስለጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ወ/ሮ ፈቲሃ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተቋሙን ሀብትና ንብረት ከብክነትና ከውድመት ለመከላከል ስልጠናው መዘጋጀቱ በሥራ አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥርላቸው እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.